Analysis of PM's Speech To The Parliment
By: Umer Abdurahaman Ethiopian Muslims Community, Riyadh, Saudi Arabia
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 10/2004
በአንዋር መስጂድ በዛሬው የጁምዓ ሰላት ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን ለሁለተኛ ጊዜ በዝምታ ገልፆአል፡፡ የአንዋር መስጂድ ኢማም የጁምዐ ሰላት አጠናቀው ሰላተል ጋኢብ ካሰገዱ በኋላ ሰጋጆቹ እጅ ለእጅ በመያያዝ እና የተለያዩ ቀለሞች ያሏቸቸውን ፕላስተሮች አፋቸው ላይ በመለጠፍ ተቃውሞአቸውን ገልፀዋል፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 10/2004
በጅማና በደሌ ከተሞች ለመስጂድ ኢማሞች በመጅሊስና በአካባቢው አስተዳደር አካላት የተዘጋጁ የስልጠና መድረኮች ላይ የተሰጡ የአቂዳ ትምህርቶች በተሳታፊዎች ተቃውሞ ተክቢራ ዛሬ መጠናቀቃቸው ተገልጾዋል፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 10/2004
በሐረር ከተማ በሚገኙ በርካታ መስጂዶች የከተማው ሕዝበ ሙስሊም የአህባሽን አስተምህሮት ያለ ፍላጎት በኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ለማስረፅ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ በመቃወማቸው ዛሬም እንወጠሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 10/2004
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊንቢና ቤጊ ከተሞች ላለፉት አስርት ቀናት ሲሰጥ በነበረው የአህባሽ አስተምህሮት ስልጠና የተሳተፉ ኢማሞች አስተምህሮቱን እንደማይቀበሉ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስልጠናቸውን አጠናቁ፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 9/2004
ነገ በጁምዐ ሰላት መጠናቀቅ በኋላ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች ምዕመናን በዝምታ ተቃውመዋቸውን ይገልፃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆዋል፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 9/2004
በአዲስ አበባ 10ሩም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች የመጅሊስ አመራሮችን የምርጫ ሂደት በሚመለከት ውይይቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሬድዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡በውይይቶቹ የመጅሊስ አመራር ምርጫ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የተለያዩ ክፍል ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ለሬድዮ ቢላል እንደስታወቁት ውይይቶቹ የተዘጋጁት በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና በዑለማዎችመ/ቤት አማካኝነት ነው፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ግንቦት 9/2004
በአሳሳ ከተማ ባለፈው ሚያዚያ 19 የተከሰተውን ሁከትና ግረግር ተከትሎ በእስር የሚገኙ 185 ሠዎች ሰሞኑን ፍርድ ቤት ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀቸው ተጠቁሟል፡፡






![]() | Today | 1245 |
![]() | Yesterday | 1806 |
![]() | This Week | 9584 |
![]() | All Days | 279654 |