በደሴ በተጀመረው የአህባሽ አስተምህሮ ስልጠና ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል መጋቢት 24/2004
በደቡብ ወሎ ዞን ርዕሰ ከተማ ደሴ ትላንት በተጀመረው የአህባሽ አስተምህሮ ስልጠና መድረክ ላይ የህዝቡ ተሳትፎ ዝቅተኛ ሆኖ መታየቱን የአካባቢው ምንጮች አስታወቁ ፡፡
ምንጮቻችን ዛሬ ከስፍራው ባደረሱን መረጃ እንዳስታወቁት ስልጠናው ትላንት በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ሲካሄድ ለተገኙት ተሳታፊዎችአረጋውያን ሲሆኑ ቁጥራቸው ከ50 አይበልጥም ፡፡ የስልጠና ጥሪውን ያስተላለፈው ለራሱ ባአደራ ኮሚቴ የሚል ስያሜ የሰጠና በከተማው ህዝበ ሙስሊም እውቅና የሌለው አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ቁጥር ከተጠበቀው በታች በመሆኑ ከደሴ ዙሪያ የገጠር ቀበሌዎች አበል እንደሚከፈላቸው የተነገራቸው ተሳታፊዎች ጭምር እንዲገቡ መደረጉን ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡
Category: Amharic News አማርኛ ዜና