በሳዑዲ የሚገኙ የመጅሊስ አመራሮች የተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በመጠናቀቁ መቸገራቸው ተገለፀ፡፡
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 4/2004
የሃጅ ጉዳይን በመፈራረም ወደ ሳዑዲ አረቢያ የተጓዙት የመጅሊስ አመራሮች በሳዑዲ ለመቆየት ተጨማሪ አንድ ወር ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡
አራት የመጅሊሱ ከፍተኛ አመራሮች የተፈቀደላቸውን የሰባት ቀን ቆይታ በመጨረሳቸው ነው ተጨማሪ ጊዜ ለአንድ ወር የጠየቁት፡፡
ይሁንና የሳዑዲ መንግስት ቪዛውን ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን እንደቀረ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ተጨማሪ የ1ወር ቆይታ ለማግኘት በሳዑዲ የኢትዮጲያ ቆንስላ ጽ/ቤት በኩል ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
አመራሮቹ የሄዱበትን ጉዳይ ሳይጨርሱ የተሰጣቸው የሰባት ቀናት ቪዛ በማለቁ ትላንት በቆንስላ ጽ/ቤቱ ውስጥ ለማደር መገደዳቸውንም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡በስፍራው የሚገኘውን የኢትዮጲያውያን ኮሚኒቲ አባላት በገጠማቸው ችግር ዙሪያ ለማነጋገር ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡
የአመራሮቹ ጥረት ያልተሳካው የኮሚኒቲ አባላቱ አትወክሉንም በሚል ለማነጋገር ፍቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
Category: Amharic News አማርኛ ዜና