የአዲስ አበባ መጅሊስ የስድስት የመስጂዶች አስተዳደር ኮሚቴዎችን ሊከስ መሆኑ ተጠቆመ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 05/08/04፣
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመዲነዋ የሚገኙ የስድስት መስጂዶች አስተዳደር ኮሚቴዎች ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን ምንጮች አስታወቁ፡፡
ውስጥ አዋቂ ምንጮች ዛሬ ለሬዲዮ ቢላል እንዳስታወቁት መጅሊሱ ክስ ለመመስረት የተዘጋጀባቸው መስጂዶች ቀደም ሲል በጠንካራ ስራዎችቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በሚያውቃቸው መስጂዶች ላይ ነው፡፡
እነዚህም የሸህ ሆጀሌ፣ የቄራ ሰላም፣ የሜክሲኮ ጀርመን ግቢ (ተባረክ)፣ የአባድር መካኒሳ፣ የባዩሽና የፈትህ መስጂዶች መሆናቸውን ምንጮች አመልክተዋል፡፡
ከፍተኛ ምክር ቤቱ ክሱን ለመመስረት የሚያስችለውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ሲሆን ሂደቱን ለማስፈፀምም ሶስት አባላት ያሉት ኮሚቴ መመስረቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የክስ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱም ሼህ አባስ ከማል፣ ሸህ ሲራጅ አንድሪስና አቶ ባርጊቾ ሁሴን መሆናቸውንም ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
Category: Amharic News አማርኛ ዜና