የዋጋ ግሽበት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ
ሚያዚያ 7/2004
ሰሞኑን በአዲስ አበባና በተለያዩ የኢትዮጲያ ክልሎች እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት አሳሳቢ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡
የዋጋ ግሽበቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የመግዛት አቅምን እያዳከመ እንደሆነ ነው እንዳንድ ሸማቾች የገለፁት፡፡
የንግድ ሚኒስቴር በበኩሉ በሀገር ውስጥ እጥረት የሚታይባቸውን መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶቻችን ከውጭ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ በስፋት እያደረሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የፍጆታ ምርቶቹን በሚፈለገው መጠን መዳረሱንና ቀድሞ ይታይ የነበረውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት መቻሉንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቀዋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ይበል እንጂ በተጨባጭ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበቱ እየጨመረ መጥቷል ነው የሚሉት ሸማቾች፡፡
በተያያዘ ዜና መንግስት በየ5ዓመቱ ዕቅድ የመጀመሪያ ዓመት አፈፃፀም ላይ የማይክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የወሰደው እርምጃ የሚበረታታ እንደሆነ የተመድ ተወካይ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋት ተወካይ ሚኒስቴር ዩጂኒ መንግስት እየወሰደው ያለው እርምጃ አበረታች ይሁን እንጂ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት ለሀገሪቷ እድገት ስጋት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
Category: Amharic News አማርኛ ዜና