የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የገንዘብ ችግር እንዳለበት ተገለፀ
ሚያዚያ 1/2004
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን የአንድ አመት የስራ ሂደት የገመገመው የአለም ባንክ ይፋ ባደረገው ረቂቅ፣ዕቅዱ እጅግ የተለጠጡ ግቦችን አንግቦ በመነሳቱ ምክኒያት ከባድ የፋይናንስ ችግር እንደገጠመው ገልፆአል፡፡
የአለም ባንክ የኢትዮጲያ ተጠሪ ጉዋንግ ዤ ቼን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የዕቅዱን አፈፃፀም ባንኩ ገምግሞ ለባለድርሻ አካላት አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት ያሰራጨው ረቂቅ ሰነድ እንደሚያረጋግጠው ከአውሮፓ አገሮች የሚገኘው እርዳታ እና ብድር ቀንሷል፡፡
ዕቅዱ በአምስት አመታት ውስጥ የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን አንድ ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከመንግስት በጀትና ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል ተብሎ ነበር የታሰበው፡፡አሁን ግን የአውሮፓ ሀገራት የተለያዩ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል የተባለው ብር አለመገኘቱ ነው የገለፀው፡፡
ይህንንም ተከትሎ መንግስት ብሩን ሊያገኝባቸው የሚችላቸውን መንገዶች ሊያጤን እደሚገባ ነው የአለም ባንክ የገለፀው፡፡
Category: International ኢንተርናሽናል ዜና አማርኛ