በአንድ ቀን 160 በሳምንት 1ሺ ሶሪያውያን መገደላቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 3/2004
የሶሪያ መንግስት ተቃዋሚ የሆነው የሶሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት በአንድ ሳምንተ ጊዜ ውስጥ አንድሺ ሶሪያውያን በፕሬዝደንት በሽር አላሳድ ወታደሮች መገደላቸውን አስታወቀ፡፡
የብሄራዊ ምክር ቤቱ ቃል አቀባይ ባሰማ ኮድማኒ የበሽር አልአሳር መንግስት ተቃውሞ የሚያሰሙ ዜጎች ባሉበት አካባቢ ጭፍጨፋና ግድያውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡
እንደ ቃል አቀባዩ ገለፃ ባለፈው ሰኞ 160 ሶርያውያን ተገድለዋል፡፡ በሲቪሎች ላይ ተደረገውን ግድያ በከባድ መሳሪያዎችና በፀረ አውሮፕላን ሮኬቶች ነው፡፡
ቃል አቀባዩም የሶሪያ መንግስት የቀረበለትን የሰላም ዕቅድ ቢቀበልም ማክሰኞ ዕለት ተግባራዊ የሚደረገውን ይህንን ስምምነት ለማደናቀፍ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ከ9ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል፡፡ የሶሪያ መንግስት በበኩሉ ለሰላም ድርድሩ የተዘጋጀ እንደሆነ ሲጠቁም በተቃዋሚዎችና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚወጣውን የሟቾች ቁጥር የተጋነነና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
Category: International ኢንተርናሽናል ዜና አማርኛ